የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ እና የጊኒ ምርጫ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 25 2018
የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ
ባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው፤ ለሞቃዲሾው የሶማሊያ መንግስትና ሀዝብ ቁጣን በሶማሌ ላንድ ሶማሊዎች ደግሞ ደስታና የድል ስሜት ፈጥሯል።ሶምሌ ላንድ
እውቅናው በሶማሊላንድ ሶማሌዎች ላይ የፈጠረው ስሜት
እ እ እ ብ1991 አም በሱማሊያ የተቀሰቀሰውን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ እራሷን ነጻ አገር አድርጋ በማወጅ የራሷን አስተዳደር መስርታ የቆየቸውን ሶማሌላንድን በይፋ በማወቅ እስራኤል የመጅመሪያዋ አገር መሆኗ ብዙ ትርጉምና ትንትና እየተሰጠው ቢሆንም ሶማሌ ላንዳውያን ግን ውሳኔውን ድፍረት የተሞላበት ትክክለኛ ውሳኔ በማለት ለእስራኤል መንግስትና ህዝብ አድናቆትና ምስጋናቸውን እያሰሙ ነው። የሶማሌላንድ ፕሬዝድነት ሚስተር አብዲራህማን ሞሃመድ አብዱላሂ ውሳኔው እንደተሰማ ለሶማሌላንድ ህዝብና ለአለም መንግስታት ጭምር ባሰሙት ንግግር፤ እለቱ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የሶማሌ ላንድ ህዝብ ሲጠይቀው የነበረው ጥያቄ መልስ ያገኘበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን ገልጸዋል “ከሶስት አስርት አመታት የሰላማዊ የራስ በራስ ማስተዳደር ልምምድ ፣ የህገመንግስታዊ ስራት ምስረታና የዴሞክራሲ ግምባታ ሂደት በኋላ ስማሊላንድ ነጻ ልዑላዊ አገር መሆኗ አለማቀፋዊ ዕውቅና አግንቷል” በማለት ይህን በማድረግ የመጀመሪያዋ ለሆነቸው እስራኤል አቅርበዋል።
በእስራኤል ውሳኔ ላይ እየተሰሙ ያሉ ውግዘቶች
የሶማሌ መንግስት ግን የእስራኤልን ውሳኔ በሶማሌ ላኡላዊነት ላይ የታወጀ ጦርነት አድርጎ ነው የወሰደውና ያወገዘው። በርካታ የመካከለኛው ምስራቅና አፍርካ አገሮች፤ ቻይናን ጨምሮ ውሳኔውን አውግዘዋል። የሶማሊያ ሉእላዊነት ሊደፈር የማይገባው መሆኑንንም አስገንዝበዋል። የአውሮፓ ህብረት፤ የአረብ ሊግ፤ የአፍርካ አንድነት ድርጅት፣ የምስራቅ አፍርካ በየነ መንግስታት ( ኢጋድም) የእስራኤል እርምጃ የአፍርካ አገሮች ደንበሮች የተካለለሉባቸውን መሰረታዊ መርሆችና ስምምነቶች የሚሽር፤ ችግሮችን ሊፈጥርና ሊያባዛ የሚችል ነው” በማለት ማስጠንቀቂያ አዘል መግለቻዎችን በየበኳላቸው አውተዋል።
ክዚህም አልፎ ጉዳዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክርቤትባለፈው ሰኞ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ክርክር ተደርጎበታል ውሳኔም ተላለፎበታል። ። በመንግስታቱ ድርጅት የሶማሊያ አምባሳደር ሚስተር አቡባከር ኦስማን በስብሰባው ላይ ባሰሙት ንግግር “ ይህ የሶማሊያ ስሜናዊ ምራቅ በሆነው ያገሪቱ ክፍል ላይ የተወሰነው ውሳኔ የሶማሊያን ግዛታዊ አንድነት የሚያፈርስ ብቻ ሳይሆን በአፍርካ ቀንድም አለመረጋጋትን የሚፍጥር ነው በማለት ምክርቤቱ የእስራኤልን እርምጃ አደገኛነት በሚገባ እንዲያጤነውና እንዲያወግዘው አሳስበው ነበር።
ያሜርካዋ ተወካይ አምባሳደር ታምይ ብሩስ በስብሰባው ባሰሙት ንግግር ግን ማንኛውም አገር የውጭ ግንኙነት ፖሊስውን በነጻነት እንደሚተገብር ሁሉ እስራኤል የራሷን የውጭ ግንኑነት ፖሊሲ የማራመድ መብት ያላት መሆኑን በመጥቀስ ውሳኔዋን ከማውገዝ ተቆጥበው፤ አሚርካ ግን የእስራኤልን ውሳኔ እንደማትከተልና በሶሚሊያ ላይ ያላት ፖሊስም ያልተለወጠ መሆኑን አስገንዝበዋል።
እስራኤል ለምን የመጀመሪያው የሶማሌ ላንድ እውቅና ሰጭ አገር ሆነች?
የሶማሌ ላንድ የእውቅና ጥያቄ ለብዙዎች የቀረበና የሚጠብቅ ቢሆንም የመጀመሪያዋ እውቅና ሰጭ አገር እስራኤል መሆኗ ግን አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ መላምቶችንና ትንታኔዎችንም የሚጋብዝ ሁኗል። እስራኤል የፍልስጤም የእውቅና ጥያቄ እያለባት፤ በጋዛ በመጠነ ሰፊ የሰባዊ መብት ጥሰት እየተከሰሰችና እየተወገዘች ባለበት ሁኔታ፤ በድንገት አፍሪካ ቀንድ ዘልቃ ለሶማሊያ ላንድ የአገርነት ጥያቄ ዕውቅና በመስጠት የመጅርመሪያዋ መሆኗ ያለምክኒያት አይድለም ነው አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኖች የሚሉት። ቀደሞ የብርታኒያ የመካክለኛው ምስራቅ ሚኒስተር የንበሩት ሚስተር ቶቢያስ ኤልዉድ እንደ ሰጡት አስተያየት ከሆነ፤ የስራኤል እርምጃ አለም ፊቱን ከእስራኤል ዘወር እንዲያደርግ ያለመ ነው። “ ከእስራኤል ውጭ እንድንነጋገርና እንድንወያይ ሆን ተብሎ የተሰጠን አጀንዳ ይመስለኛል። ካልሆነ እጅግ ብዙ ችግሮች እያሉባት ለምን ሌላ አወዛጋቢ የውጭ ፖሊሲስ ታርምዳለች? ውሳኔው አጀንዳ ለማስቀየር፤ በእስራኤል፤ ጋዛና የምራብ ዳርቻ እየሆነ ካለው አይናችንን እንድናነሳ ለማድረግ ያለመ ሊሆን ይችላል” በማለት ከእስራኤል የሶማሌ ላንድ እውቅና ጀርባ ይኖራል ያሉትን የእስራኤል እሳቤ አመላክተዋል።
ከኦስሎ ሶማሊያዊው የፖልቲካ ተንታኝ ሚስተር ሞሃመድ ኬይር ኦመር ደግሞ የእስራኤል ውሳኤ በሁለት ዋና ዋና ምክኒያቶች ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል ድምስ “በሁለት ምክኒያቶች ሊሆን ይችላል፤ አንዱ የሶማሌላንድ የጆግራፊያዊ አቀመማጧና በቀይባህር ደባብዊ መግቢያ ላይ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው፤ የአፍርካ ቀንድ ብዙ ችግሮች ያሉበትና በርካታ ተዋንያን ያሉበትም መሆኑ ነው በማለት ውሳኔው ሁለቱንም በሚጠቅም ስምምነ ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
እስራኤል እውቅና የሰጠችባቸው ምክኒያቶች፤ በሶማሊያው ፕሬዝደንት አስተያየት
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ግን የእስራኤል ውሳኔ የተላለፈው ከሶማሌ ላንድ ጋር በሶስት ጉዳዮች ተስማምተው ነው፤ “አንደኛው፤ ፍልስጤማውያንን በሶማሊያ ላንድ የማስፈር አጀንዳ ነው። ሁለተኛው በኤደን የባህር ሰላጤ እስራኤል የጦር ሰፈር እንዲኖራት መፍቀድ ሲሆን ሶስተኛው ሶማሌ ላንድን እስራኤልን በወዳጅነት ከሚቀበለው የአብረሀም ስምምነት እንድትቀላቀል ነው” በማለት ይህ ስለመሆኑ አስተማማኝ መረጃ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የሶማሌ ላንድ ሁኔታ በሌሎች አገሮች ከሚነሱ የመገንጠል ጥያቄዎች ጋር አይመሳሰልም መባሉ
በሌላ በኩል ግን የሶማሌ ላንድ ጥያቄ በሌሎች አገሮች ከነበሩ ወያም ካሉና የመገንጠልን ጥያቄ ከሚያራምዱ ግዛቶች ወይም ህዝቦች አንድ አይነት እንዳልሆነ መረዳትታ እንደሚያስፈልግ ነው የሚንገረው፡፤ ሶማሊያ ላንድ እራሷን ከሶማሊያ ነጥላ ማስተዳደር ከጀመረችበት ከ 1991 ጀምሮ መንግስታዊ መዋቅሮችን በመዘርጋትና ተቋማትን በመገንባት፣ የራሷን ሰራዊትና የፖሊስ ሀይል በማደራጀትና ሰላምና ደህንነቷን በራሷ በማስከበር፤ እንዲሁም ዴሞክራዊ ምርጫውፕችን በማካሄድና ሰላማዊዊ የስልጣን ሽግግር በማደረግ በኩል በአካባቢው በአራያነት የምትጠቀስ ናት የሚሉ ወገኖች፤ ባንጻሩ የሞቃዲሾው መንግስት እስካሁንም ያልተረጋጋና በእገሪቱ ላይም ሙሉ ቁጥጥር የሌለው መሆኑ የሶማሌ ላንድን ጥያቄ ምክኒያታዊ አያደረርገውም ወይ በማለት ይጠይቃሉ።
የሶማሌ ፕሬዝዳንት የውጭ ግንኙነት አማካሪ ዶክተር ሞህመድ ሃጂም በዚህ በኩል አገሮች የሱማሌ ላንድን ልዩ ሁኔታ ማወቅና መረዳት እንዳለባቸው ነው የሚያሳስቡት “ ሶማሊ ላንድ ነጻነቷን ያገኘችው እ እ እ በ 1960 አም ነው። ወዲያውም ክሶማሊያ ጋር በፈቃደንነት ተቀላቅላ የነበር ሲሆን እ እ እ ብ1991 ዓም ግን እንደገና ነጻነቷን አቅግንታለች በማለት በዚህም ምክኒያት ሶማሊያ ላንድ የሶማሊያ አካል ናት ማለት ስህትት እንደሆነንና ከሶማሊያ ጋር አዛምዶ ማየትም ትክክል እንዳልሆነ መረዳት እንደሚገገባ አስገንዝበዋል ።
እውቅናው በሶማሌ ላንድ ላይ የሚኖረው አንደምታ
ይህ በብዙ ተቃውሞና ውግዘት የታጀበው የእስራኤል የሶማሌ ላንድ እውቅና በተለይ በሶማሌ ላንድ አለማቀፍ የእውቅና ጥያቄ ላይ ከፍተኛ አንደምታ እንዳለው ነው በሶማሌ ላንድ ሶማሌዎች የሚታመነው። የሶማሌ ላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር አብዲራህማን ዳሂር አዳም ይህንን ሲያብራሩ ፤ የእስራኤል የሱማሌ ላንድ እውቅና በተምሳሌንቱ ብቻ ሳይሆን በተግባር ትልቅ ጥቅም ነው ያለው። የሶማሌ ላንድ ያገርነት እውቅና ጥያቂ ህጋዊ መሰረት ያለውና የልዑላዊ አገርነት መስፈርቶንን ያሟላ መሆኑን ያረጋገጠ ነው። በተጨባጭም የኛን ጥንካሬና ያገሪቱን ተአማኒንነት ያሳየም ነው። የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ለማድረግ ይረዳል፤ ኢንቨስተሮችንም ይስባል፤” በማለት አገሮች በሶማሌ ላንድ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ሊያስወግዱ እንደሚገባም አሳስበዋል
ይሁን እንጂ የተቃውሞ ዘመቻው እንደቀጠለ እየተስተዋለ ነው፡፤ በተለይ ቱርክ የሶማሊያን ሉእላዊነት ለማስከበር ሁሉንም ነገር እንደምታደርግ እየገለጸች ሲሆን፤ ግብጽና ሶኡዲ አረቢያ፤ ኤርትራና ጂቡቲም ጭምር ከተቃውሞው ጎራ መሰለፋቸው ታውቋል።
በቤሌላ በኩል ደግሞ እስራኤል በአካባቢው መገኘቷ የየመን ሁቲዎችን እንቅስቅሴ ለመቆጣጠርና ከሁሉም በላይ የኢራንን አካባቢው ተጽኖ ለመግታት እስከሆነ ድረስ በተለይ ሳኡዲ አረቢያና አሚሪካ ተቃውሞ ሊኖራቸው እንደማይችል የሚገምቱ ታንታኖች፤ ይልቁንም በቀጣይ የሶማሌ ላንድን አገርነት የሚቀበሉ አገሮች ከሩቅም ክቅርብም መምጣታቸው አይቀርም ይላሉ።
የጊኔ ወታደራዊ መሪ አሸናፊ የሆኑበት የጊኒ ምርጫ
በምዕራብ አፍርካዊቷ አገር ጊኒ ባለፈው ሳምንት በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እ እ እ በ2021 አም በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት ጄነራል ማማዲ ዱንቦያ በከፍተኛ ድምጽ ያሸንፉ መሆኑን ያገሪቱ የምርጫ አስፍጻሚ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ሆኖም ግን ምርጫው ነጻና ግልጽ እንድልነበርና፤ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎችም ክውድድር የታገዱበት የይስሙላ ምርጫ እንደንበር ነው ሲቪል ማህብረሰቦችና የምርጫ ታዛቢዎች የገለጹት። ጀኔራል ዱንቦያ እ እ እ እ በ2021 ዓም ያኔ የ83 አመት አዛውንት የነበሩትን ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በመፈንቅለ መንግስት ያስወገዱት በአገሪቱ ሙስና በመንሰራፋቱ፣ መልካም አስተዳደር በመጥፋቱና የአገሪቱ ኢኮኖሚ በማሽቅልቆሉ በመሆኑ እንደሆነ ሲገልጹ የነበር ቢሆንም ባለፉት አራት አመታት የርሳቸው የስልጣን ዘመንም ግን ብዙም የተለወጠ ነገር እንደሌለ ነው የሚገለጸው። እንደውም ፕሬአዳንቱ ባለፉት አራት አመታት የተቃውማዎችን እንቅስቅሴ በመግታት፤ ተቃውሞን በመገደብና ፕሬሱን በማፈን በብዛት ሲተቹ ቆይተዋል።
ከሁሉም በለይ ግን ጀነራል ዱምቦያ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት “ኤኔም ሆንኩ ሌሎችየወታደራዊ አስተዳደሩ አባሎች አንዳችንም ወደፊት በሚደረገው ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ሆነን ለምርጫ ስንቀርብ አታዩንም” በማለት የተናገሩትን የሚያስታውሱት ጊናያውያን የነበራቸው ተስፋ እንዲያሟጠጥ እንዳደርጋቸው ነው የሚነገረው።፡
ጊኒን ጨምሮ በብዙዎች የመእራብና መካከለኛው ዓፍርካ አገሮች በወታደራዊ መፈንቅለ መንግት ወደ ስልጣን መውጣትና መውረድ የተለመደ ሲሆን፤ እ እ እ ከ2021 አም በኋላ ብቻ እንኳ አስር መፈንቅለ መግስቶች ተካሂደዋል።
በጊኒም በመፍንቅለ መፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጡ ባሁላ ቃላቸውን አጥፈው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው አሸነፉ የተባሉት የ41 አመቱ ጎልማሳ ጄኔራል ማማዲ ዱምቦያ በአዲሱ ሀገመንግስት መሰረት ምናልባትም በሳቸውም ላይ መፈንቅለ መንግስት ካልተካሄደባቸው በስትቀር ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሰባት አመታት በስጣልን ላይ የሚቆዩ ይሆናል።
ጊኒ በዓለም ከፍተኛ የቦክሳይትና የብረት ማዕድኖች ክምችት ያለባት አገር ብትሆንም የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚያሳየው ግን ከ6 ሚሊዮኑ ህዝቧ ግማሽ ያህሉ በድህነት የሚኖር ነው።፡
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ