የእስራኤል ዕውቅና ያስከተለው ተቃውሞና ውግዘት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2018
የእስራኤል ዕውቅና ያስከተለው ተቃውሞና ውግዘት
እስራኤል ለሶማሊ ላንድ የሰጠችው እውቅና በልኡላዊ ግዛት ላይ የታወጀ ጦርነት አድርጎ ነው የወሰደው። በርካታ አገራትና አህጉራዊ ድርጅቶችም የእስራኤል ውሳኔ የሶማሌን ሉላዊነት የሚጥስ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላውበአካባቢው ችግር የሚፈጥርና ቀውስ ያሚያስከትል በመሆኑ አንደምታው ከሶማልያ ሊያልፍ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው።፡ በናይሮቢ የአፍርካ ቀንድ የስታሬተጂ ጥናት ማዕከል ዳይሬተር የሆኑት ዶክተር ሀሳን ክሀኔን ጄ የውሳኔውን አንደምታ እንዲህ ነው የገለጹት ።
” ውሳኔው ከፍተኛ አንደምታ ያለው ነው። ለሶማሌላንድ የነጻነት ጥያቄ አንድ ርምጃ ሊሆን ይችላል በሌላ በኩል ደግሞ ውሳኔው በአፍሪካ ባጠቃላይ ግን ደግሞ በፍርካ ቀንድ የድንበር ለውጥ ጥያቄዎችን ሊያመጣና ነባሩን የቅኝ ግዛት ድንበሮችን የማክበር ያልተጻፈ ሕግ የሚሽር ሊሆን ይችላል” በማለት ውሳኔው ዘርፈ ብዙ ችግሮችንም ሊያስከትል እንደሚችል ገልጸዋል።
አህጉራዊ ድርጅቶችም የእስራኤልን ርምጃ በማውገዝ የሶማሊያ ሉላዊነትና የግዛት አንደንት መከበር ያለበት መሆኑን አሳስበዋል። የአረብ ሊግ፣ የአፍርካ እንድነት ድርጅትና ያአውሮፓ ህብረት በየበኩላቸው ባወጧቸው መግለጫዎች የእስራኤል ርምጃ አለማቀፍ ሕግን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ፤ በተለይም ግጭትና ሁከት ተለይቶት ለማያውቀው የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ቀውስ የሚፈጥር ነው” በማለት አውግዘዋል። የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ የሶማሊያን አንድነት የሚያከበር መሆኑን ጠቅሶ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ አሳስቧል።
እስራኤል የሶማሊያ ላንድን አገርነት በማወቅ ለምን የመጅመሪያዋ ሆነች
እስራኤል ለሶማሌ ላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያ መሆኗ እራሱ ብዙዎችን የሚያነጋግርም ሆኗል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ከሶማሊላንድ ጋር በኢኮኖሚ በግብርናና ሌሎች ዘርፎች በጋራ ለመሥራት አገራቸውና መንግሥታቸው ዝግጁ መሆናቸውን ቢገልጹም ዋናው ምክንያት ግን ከዚህ ሊዘል እንደሚችል ነው ተንታኖች የሚናገሩት።
በፕሪቶሪያ ዩቨርስቲ የዓለማቀፍ ግንኙነትና የግጭት ማስወገድ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ኪንግስሌይ ማክሁቤላም እስራኤልን ወደ አፍሪካ ቀንድ ያመጣት ሌላ አጀንዳ ሊኖር እንደሚችል ነው የሚናገሩት። “ ዋናው ነገር በባብል መንደብ በኩል ወደቀይ ባህር የመዝለቅ ወይንም በዚያ አካባቢ የመገኘት ፍላጎት ነው። ለእለራኤል በቀይ ባህር ላይ ባለድርሻ መሆን ትልቅ ነገር ነው። ምክንያቱም የቀይ ባህር መዳረሻ የሆነው ባብል መንደብ ባንድ በኩል በጅቡቲና ኤርትራ፤ በሌላ በኩል በየመን ሁቲዎች የሚዋሰን ሲሆን፤ እስራኤል በሀርጌሳ በኩል በአካባቢው ላይ ተጽኖ እንዲኖራት ትፈልጋለች” በማለት ወደዚህ የመጣችውም የባህር ላይ ስትራቴጂዋ በዚህ አካባቢ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላላ በሚል ስጋት ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ማንተጋፍቶት ስለሺ