1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የርዳታ አሰጣጥ መርሕ እየተጣሰ ነዉ-አመልድ

ኢሳያስ ገላው
ዓርብ፣ ጥር 1 2018

ድርጅቱ፣ በአንዳንድ አካላት አማካኝነት "የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር"፣ "እምነት" እና "ሞራል" ባልጠበቀ መልኩ ሰብዓዊ ድጋፎችን "የእምነት ማራመጃ" እና "ማስፋፊያ" መሣሪያ አድርጎ የመጠቀምና ተረጂዎችን ለተጽዕኖ የመዳረግ አሰራሮች መስተዋላቸው እጅግ አሳሳቢ ብሏል

https://p.dw.com/p/56bgW
አመልድ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት እንደሚለዉ አንዳድ ድርጅቶች ሰብአዊ ርዳታን አላግባብ ለእምነት ማስፋፊያ እያዋሉት ነዉ
ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል ከሠፈሩ ኢትዮጵያዉያን በከፊል ርዳታ ሲጠባበቁምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የርዳታ አሰጣጥ መርሕ እየተጣሰ ነዉ-አመልድ

 

አመልድ ኢትዮጵያ‎ የተሠኘው የቀድሞው የአማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት፣ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች "የሰብዓዊ እርዳታ አሰጣጥ  መርሆዎችን" የሚጥሱ ተግባራት ይታያሉ ሲል  ባወጣው መግለጫ ወቀሠ።ድርጅቱ፣ በአንዳንድ አካላት አማካኝነት "የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር"፣ "እምነት" እና "ሞራል" ባልጠበቀ መልኩ ሰብዓዊ ድጋፎችን "የእምነት ማራመጃ" እና "ማስፋፊያ" መሣሪያ አድርጎ የመጠቀምና ተረጂዎችን ለተጽዕኖ የመዳረግ አሰራሮች መስተዋላቸው እጅግ አሳሳቢ  ብሏል።ዕርዳታን የእምነት መሳሪያ ያደረጉ አካላትንም ሆነ  ወይም ድርጊቱ የተፈፀበትን ሥፍራ ግን አልጠቀሰም።

ሁሉም በጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት እና ለጋሽ ተቋማትሰብአዊ መርሆችን የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ባለፉት 40 ዓመታት በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ የሚታወቀውአመልድ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል አንዳንድአካባቢዎች የእርዳታ አሠጣጥ መርሆችን የሚጥሱ  ተግባራትይታያሉ ያለው የአመልድ መግለጫ ድርጅቶቹ የዜጎችን ችግርእንደ አጋጣሚ በመጠቀም ይፈፅማሉ ያላቸውን ችግሮችዘርዝሯል፤ ሀይማኖት የማስቀየር፣ የተረጅዎችን ክብር መንካት፣ ከፍተኛ የሞራል ግድፈቶችን በእርዳታ ስም መከወናቸውንድርጅቱ አውግዟል፡፡ አመልድ ኢትዮጵያ አለምአቀፍ መስፈርቶችእንደሚደነግጉት ሰብዓዊ ርዳታ ያለምንም ሀይማኖታዊ ወይምብሔር ተኮር ጫና መቅረብ አለበት ይላል፡፡ በዚህ ዘርፍሃሳባቸውን እንዲያጋሩ የጠየኳቸው በአማራ ክልል የሚገኙየሲቪል ሶሻይቲዎች ህብረት ለትብብር እና ልማት ዳይሬክተር አቶንጋቱ ደስታ የረድኤት ተቋማት የተመሰረቱበትን አላማ ማክበርይጠበቅባቸዋል ይላሉ፡፡

‹‹መርሁ የሚለው የረድኤት ተቋማት ከፖለቲካ፣ ከሀይማኖትገለልተኛ ናቸው፡፡ አስቼኳይ ርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜም ሆነሀይማኖትን ፣ዘርን፣ እምነትን መሰረት ሳያደርጉ ማገዝ ነው መርሁ፤ ይህንን የማያደርጉ ካሉ ከመርሁ የወጡ ናቸው፡፡›› 

የሰብአዊ ርዳታ ያለምንም ሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ ወይም ብሔርተኮር ጫና መቅረብ አለበት ያለው አመልድ ኢትዮጵያ የተባበሩትመንግስታት ድርጅት ስምምነቶች በግልጽ እንደሚያስቀምጡትማንኛውም ግለሰብ የለሹን እምነት ወይም ሀይማኖት እንዲቀበልሳይገደድ ርዳታ የማግኘት መብት አለው ይላል የአመልድመለግጫ፤ በአንድ የረድኤት ተቋም ዳይሬክተር የሆኑ አስተያየትሰጭም በእንደዚህ አይነት ከረድኤት ተግባር አላማ ጋር ያልወገነንተግባር የሚፈፅሙ ድርጅቶች ካሉ መንግስት ዝም ማለትየለበትም ብለዋል፡፡ 

 

‹‹አሁን እምነትን ታሳቢ ተደርጎ እርዳታ የሚሰጥ ከሆነ ከመርሁውጭ ያሉ ተቋማትን መያዝ ነው፡፡ በህግ መጠየቅ፣ መቅጣትነው፡፡ የሲቪል ሶሻይቲ ተቋማት ምን እንደሚሰሩ፣ አላማው ምንእንደሆነ፣ ምን እንደሚተገብሩ ግልጽ ነው፡፡ እዛ ውስጥ የሚሳተፉካሉ ፈቃዳቸውን መሰረዝ አለያም አስፈላጊ ከሆነ ማስጠንቂያመስጠት ያስፈልጋል፡፡›› 

 

ከ20 ዓመት በላይ በመሰል የረድኤት ተግባር ላይ የተሰማሩት ወ/ሮ ሀኒያ መሀመድም የሲቪክ ተቋማቶች ለትርፍ ያልተቋቋሙበመሆናቸው የገቡትን ቃልኪዳን አቅርበው የመስራት ግዴታአለባቸው ይላሉ፡፡‹‹ተቋማችን ለትርፍ ያልተቋቋመ ገለልተኛ፣ ከሀይማኖትምከምንም ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ ነው፡፡ ይህ ቃል ኪዳናችን  ነው፡፡ ሰውን በሀይማኖቱም፣ በሌላም ላትለይ ነው ፤ ይህ የተቋቋምንበትአላማ ነው፡፡›› 

አመልድ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት እንደሚለዉ አንዳድ ድርጅቶች ሰብአዊ ርዳታን አላግባብ ለእምነት ማስፋፊያ እያዋሉት ነዉ
በአማራ ክልል ለሠፈሩ ተፈናቃዮች የሚከፋፈል የርዳታ እሕል በከፊልምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

 

83 የረድኤት ተቋማት በስሩ አቅፎ የሚንቀሳቀሰው ህብረትለትብብር እና ልማት ዳይሬክተር እንደሚሉት አሁን አመልድኢትዮጵያ ያቀረበውን ሃሳብ በጥናት ተጨባጭ የማድረግ ስራህብረቱ እንደሚጠበቅበት ገልፀው መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛድጋፍ እያደረገ በመሆኑ የሲቪል ሶሻይቲዎች የራሳቸውን ምክርቤት እንዲያቋቁሙ በመፍቀዱ በዚህ አይነት ተግባራት ላይየሚሳተፉ ካሉ ከአባልነት ማገድ እና መንግስትም ጠበቅ ያለርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል ይላሉ፡፡ ‹‹መንግስት በደንብ መስመር ማስገባት አለበት፤ ሲቪል ሶሻይቲምክር ቤት ወደ መንግስት ከመሄዱ በፊት የራሱን አባላት ከህጉሲወጡ የሲቪል ሶሻይቲ መርህ አይደለም ብሎ ማስጠንቀቂያይሰጣል፤ ከአባልነት ያግዳል፤ በመንግስትም ርምጃ ይወሰድባቸውብሎ ያቀርባል፤፡›› 

 

አመልድ ኢትዮጵያባወጣው መግለጫ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃእንዲሰጡኝ ወደ ዳሬክተሩ    ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ደውየ የነበረቢሆንም ሃሳባችንን በጽሁፍ ገልፀናል ሲሉ ተጨማሪ መረጃለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ 

ኢሳያስ ገላዉ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ