1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትራምፕ አስተዳደር ርምጃና መርሕ፣የተቀረዉ ዓለም ሥጋት

ዓርብ፣ ጥር 1 2018

የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም ይጎዳል የሚሉትን ሐገር፣መሪ፣ይሁን ድርጅት በኃይል ጭምር እያስወገዱ የአሜሪካንን ጥቅም ያስከብራል የሚሉትን እየገነቡ ነዉ።የቬኑሱዌላን መሪ ባሳገቱ ማግሥት ግሪንላንድ የተባለችዉን የዴንማርክን ግዛት ለመጠቅለል ዳግም እየዛቱ ነዉ

https://p.dw.com/p/56bHg
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የ,ዴንማርክን ራስ ገዝ ግዛት ግሪንላንድን ለመጠቅለል እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ አስታዉቀዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሚቀጥለዉ ትኩረታቸዉ ግሪንላንድን «መቀማት» ይሆን?ምስል፦ Federico Parra/Odd Andersen/AFP

የትራምፕ አስተዳደር ርምጃና መርሕ፣የተቀረዉ ዓለም ሥጋት

 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ«አሜሪካ ትቅደም» የሚል መሠረታዊ መርሐቸዉን ተራ በተራና በግልፅ ገቢራዊ እያደረጉ ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም ይጎዳል የሚሉትንሐገር፣መሪ፣ይሁን ድርጅት በኃይል ጭምር እያስወገዱ የአሜሪካንን ጥቅም ያስከብራል የሚሉትን እየገነቡ ነዉ።የቬኑሱዌላን መሪ ባሳገቱ ማግሥት ግሪንላንድ የተባለችዉን የዴንማርክን ግዛት ለመጠቅለል ዳግም እየዛቱ ነዉ።ትናንት ዩናይትድ ስቴትስ አባል ከነበረችባቸዉ ከ66 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንድትወጣ ትራምፕ ወስነዋል።አዉሮጳን ጨምሮ የትራምፕ እርምጃና ዉሳኔ ያስደነገጠዉ ዓለም ከመገናኛ ዘዴዎች መግለጫ ባለፍ የዓለም ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር አቅመቢስ መሆኑን በግልፅ እያሳየ ነዉ።በዚሕ ጉዳይ ላይ ከገበያዉ ንጉሴ ጋር አጭር ዉይይት አድርገናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ