1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አጋርነት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2018

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች "አንዳቸው የሌላኛቸውን ሰላም እና ደኅንነት" "የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ" ያላቸውን ስልታዊ አጋርነት በድጋሚ ማረጋገጣቸዉ ተሰማ። የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ "ቀጣናዊ መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት" ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸዉን አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/56TmG
Äthiopien Addis Abeba 2026 | Außenminister Timothewos mit Minister Scheich Schachbut Bin Nahjan
ምስል፦ The Ethiopian Ministry of Foreign Affairs

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች "አንዳቸው የሌላኛቸውን ሰላም እና ደኅንነት" እንዲሁም "የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ" ያላቸውን ስልታዊ አጋርነት በድጋሚ ማረጋገጣቸዉ ተሰማ። የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ "ቀጣናዊ መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት" ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸዉን አስታዉቀዋል።

ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶቹ ትናንት  ታኅሣሥ 28/2018 ዓ.ም የጋራ መግለጫውን ያወጡት፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሥራ ጉብኝት ተከትሎ ነው።

የአቡዳቢው ሚኒስትር ዲኤታ፤ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ተገናኝተው "ቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት" ላይ የጋራ ፍላጎትታቸዉ ላይ ተወያይተዋል። 

ዶ/ር ጌዲዮን እና ሼህ ሻክቡት ከሁለትዮሽ ጉዳዮችም በተጨማሪ "በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ የተመዘገቡ ቁልፍ ለውጦችን" እንደገመገሙ መግለጫው ያስረዳል።

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ