በጎርጎሪዮሱ 1954 የተመሠረተው የአውሮጳ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት (UEFA) አውሮጳ ውስጥ የእግር ኳስ የበላይ አካል ነው ። ሻምፒዮንስ ሊግን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ተመልካች ያላቸው የእግር ኳስ ውድድሮችን ያዘጋጃል። ተቋሙ 55 ብሔራዊ ማኅበራትን በአባልነት ያቀፈ ነው።