1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርትኢትዮጵያ

በሳምንታት መጨረሻ የሚሰጡ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ጥቅማቸው ወይስ ጉዳታቸው ያመዝናል?

ሥዩም ጌቱ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 2018

ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ማሽቆልቆሉን ተከትሎ መንግሥት የተለያዩ የትምህርቱ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ነው። የዚህ ትምህርት ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?

https://p.dw.com/p/55kVx
ተማሪ ዴሊና ዳዊት እና ተማሪ ብሌን ጎይቶም ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ጋር
ተማሪ ዴሊና ዳዊት እና ተማሪ ብሌን ጎይቶም ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ጋርምስል፦ S. Getu/DW

የማጠናከሪያ ትምህርቶች ጥቅማቸው ወይስ ጉዳታቸው ያመዝናል?

ተማሪዎች ዋናውን ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ እንዲያደርጉ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲገደብ እና ተማሪዎች በፍጹም ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚያግደው እርምጃ አንደኛው ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ተማሪዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀን በተለይም ቅዳሜ ቅዳሜ ወደ ትምህርት ቤት በማቅናት የማጠናከሪያ ትምህርት በመውሰድ ያለፉትን ክፍሎች ትምህርት በጥያቄ መስራት እና በልዩ ልዩ መንገድ እንዲከልሱ የሚያደርገው መርኃ ግብር ነው፡፡
ይህ የሳምንቱ መጨረሻ የማጠናከሪያ ትምህርት በተማሪዎች ዘንድ የተለያየ ቀበሌታ አለው።


ከፊል ተማሪዎች ይህ የሳምንት መጨረሻ የማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎች ያለፉባቸውን ትምህርቶች በማስታወስ ጥያቄዎችን በመስራት ክለሳ እንዲያደርጉ እና በመጪው ብሔራዊ ፈተናቸው ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ይረዳሉ፡፡
ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ በአምስቱ የስራ ወይም መደበኛ ቀናት ከሚሰጠው ትምህርት በተጨማሪ በእረፍት ቀናቸው ተብሎ በሚታሰበው ቅዳሜ የሚሰጠው ተጨማሪ ትምህርት ተማሪዎች ሊያገኙት የሚገባቸውን እረፍት በመንፈግ አላስፈላጊ መጨናነቅን ይፈጥራል በሚልም የሚረዱ አሉ፡፡

ተማሪ ዴሊና ዳዊት እና ተማሪ ብሌን ጎይቶም ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ጋር
ተማሪ ዴሊና ዳዊት እና ተማሪ ብሌን ጎይቶም ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ጋርምስል፦ S. Getu/DW


እነዚህ ተማሪዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት አስፈላጊ ለሆነው መዝናኛ፣ ለሃይማኖታዊ ተግባራት፣ ለማህበራዊ ግንኙነት እና የጎንዮሽ ተስእጦን ለማሳደግና ለማዳበር የሚረዳውን የሳምንታት መጨረሻ ቀናት የማጠናከሪያ ትምህርት መርኃግብሩ እንደሚሻማባቸው ነው የሚያስረዱት፡፡
በማጠናከሪያ ትምህርቱ አስፈላጊነት የሚያምኑቱ ተማሪዎች በፊናቸው፤ ካለፉት ዓመታት የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆልና ውድቀት በመማር የተሻለውን ጊዜያቸውን ለትምህርት በመስጠት ውጤታማ ለመሆን መንገድ ጠራጊ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው በሚል ያነሱታል፡፡
በዚህ ሃሳብ ላይ የዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች መሰናዶ ሁለት ታዳጊዎችን አከራክሯል። ተወያዮቹ
የ11ኛ ክፍል ተማሪዋ ዴሊና ዳዊት እና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ብሌን ጎይቶም ሲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርት መርኃግብርን በመደገፍና በመንቀፍ ሃሳቦቻቸውን አንሸራሽረዋል፡፡


አወያይ፤ የዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል