1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ስደተኞች በአሜሪካና በአውሮፓ የገጠማቸው ፈተና

እሑድ፣ ታኅሣሥ 19 2018

ከ5ሺህ በላይ ይሆናሉ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ድንገት ወደሀገራቸው እንዲሚመለሱ ተነግሯቸዋል። ኢትዮጵያውንንም ተጠቃሚ ያደርግ የነበረው ቋሚ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሚያስገኘው የDV መርሃ-ግብር መቋረጡ ተነግሯል። እነዚህ ስደተኞችን የሚያዋክቡ አሰራሮች ወደ አውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራትና ብሪታንያም ጭምር የመዛመታቸው አዝማሚያ ያሰጋል።

https://p.dw.com/p/560FA
ተሰዳጆችን የሚይዙ  ICE ፖሊሶች
ተሰዳጆችን የሚይዙ ICE ፖሊሶች ምስል፦ Michael Nigro/Pacific Press/picture alliance

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ስደተኞች በአሜሪካና በአውሮፓ የገጠማቸው ፈተና

የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ፣ የስደተኞች አስጠጊ ፣ ለተበደለ የሚቆም ሆኖ ይታይ የነበረው ምዕራቡ ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ አቋሙ የተቀየረ ይመስላል። እነዚህ ባለፀጋ አገራት ፣ደጃቸውን ጠርቅመው፣ የቀድሞው ቸርነታቸው በእጅጉ ርቆ መሄጃ ያጣ፣ መድረሻ የሌለውን መጻተኛ እንኳን አንይ ካሉ ሰነበቱ። ይህ ብቻ አይደለም አሁን አሁን ለዓመታት ሀገራቸውን ሀገሩ አድርጎ የሚኖረውን የውጭ ዜጋ ማሸማቀቅ ጭምርም ይዘዋል። እነዚህ ድርጊቶችም በልዕለ ኃያሏ ዩናይትድ ስቴትስ ገሀድ ወጥተዋል። በስደተኞች ጫንቃ በተገነባችውአሜሪካ፣ ለአገሪቱ ብዙ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የሚነገርላቸውን ስደተኞችን ፣የሚጠቅሙ ሕጎች በሰብ አስባቡ አሳማኝ በማይመስሉ ምክንያቶች እየተሰረዙ ፣የማያፈናፍኑ አስጨናቂ እርምጃዎችም ተግባራዊ በመሆን ላይ ናቸው።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትዶናልድ ትራምፕ ሕገ ወጥ የሚባሉ ስደተኞችን ብቻ ሳይሆን በሕጋዊ መንገድ አሜሪካን ገብተው ዜግነት ካገኙት  ከተወሰኑ ሀገራት ለሆኑትን ጭምር የተለያየ ስም በመስጠት መዝለፍ ማንቋሸሽ ማጣጣላቸውም ቀጥሏል። ይህም በሀገሪቱ ተገን ለማግኘት የሚጠባበቁትን ብቻ ሳይሆን ኑሮአቸውን ለዘለቄታው አሜሪካን ባደረጉ የውጭ ዜጎች ላይ ግርታና ብዥታ ፈጥሯል። ከነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይገኙበታል።

በቺካጎ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተካፋይ የነበረ ሰልፈኛ በICE ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ
በቺካጎ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተካፋይ የነበረ ሰልፈኛ በICE ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ ምስል፦ Nam Y. Huh/AP Photo/picture alliance

ቁጥራቸው ከ5ሺህ በላይ ይሆናል የተባሉ ኢትዮጵያውያን ድንገት ወደሀገራቸው እንዲሚመለሱ ተነግሯቸዋል። ኢትዮጵያውንንም ተጠቃሚ ያደርግ የነበረው ቋሚ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሚያስገኘው የDV ሎተሪ መርሃ-ግብር መቋረጡ ተነግሯል። ይህን መሰሉ ስደተኞችን የሚያዋክብና ጭንቀት ላይ የሚጥል አሰራር ወደ አውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራትና ብሪታንያም ጭምር የመዛመቱ አዝማሚያ ያሰጋል።

 የዛሬው እንወያይ «ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ስደተኞች በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካና በአውሮፓ የገጠማቸው ፈተና? ላይ ያተኩራል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል። እነርሱም ዶክተር ቃለ አብ ካሳዬ በሲያትል ዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ባለሞያ እና ጠበቃ ፣ አቶ ዳንኤል መለሰ ንጋት ኢኒሽየቲቭ የተባለ በፍልሰት አስተዳደርና ችግሮቹን በመከላከል ላይ የሚሰራ ድርጅት መስራችና ሃላፊ ፣ድልነሳው ጌታሁን የቴሌቪዥን ባለሞያና የዶቼቬለ ዘጋቢ ከለንደን ናቸው።

ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ 

ኂሩት መለሰ 

ታምራት ዲንሳ